የካድስተር መረጃ አያያዝ ስርዓት ዝርጋታ ፕሮጀክት ትውውቅ ተደረገ

የካድስተር መረጃ አያያዝ ስርዓት ዝርጋታ ፕሮጀክት ትውውቅ ተደረገ

በኢትዮጵያ ኢነርጂ ባለስልጣን በጂኦተርማል ሀብት ልማት ፈቃድ ማስተዳደር ዳይሬክቶሬት የካድስተር መረጃ አያያዝ ስርዓት ዝርጋታ ፕሮጀክት ትውውቅ ተደረገ፡፡ በፕሮጀክት ትውውቁ ላይ የክልል ኢነርጂ ቢሮ ተወካዮች እና ከተለያዩ የፌድራል መንግስት መ/ቤቶች የመጡ ተሳታፊዎች ተገኝተዋል፡፡ የፕሮጀክቱ መጀመር የመረጃ አሰጣጥ ስርዓቱን ፈጣን እና ቀልጣፋ እንደሚያደርገው የተገለፀ ሲሆን በዘርፉ ለመሰማራት ለሚፈልጉ ኢነቨስተሮች ግልጽነት ያለው የመረጃ አሰጣጥ እንዲያገኙ እንደሚያግዛቸው ተገልጧል፡፡ በተጨማሪም የኢነርጂ ለተሳታፊዎች የኢነርጂ ብቃት ፕሮግራምን አስመልክቶ ገለጻ ተደርጎላቸዋል፡፡


Print   Email