በመንዝ መሀል ሜዳ አነስተኛ የንፋስ ሀይል ተጠቃሚ ነዋሪዎች እና አገልግሎት ሰጪ ተቋም ጋር ውይይት ተደረገ

በመንዝ መሀል ሜዳ አነስተኛ የንፋስ ሀይል ተጠቃሚ ነዋሪዎች እና አገልግሎት ሰጪ ተቋም ጋር ውይይት ተደረገ
በባለስልጣን መ/ቤቱ የተቋቋመ ኮሚቴ በኢትዮሪሶርስ ግሩፕ እና ከመንዝ መሀልሜዳ ነዋሪዎች ጋር ከግሪድ ውጪ በሚሰጥ የመብራት አገልግሎት ጋር በተያያዘ ውይይት አድረጉ፡፡
ከቤሄራዊ ግሪድ ርቀው ለሚገኙ የአከባቢው ነዋሪዎች የመብራት ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችል ከአነስተኛ የንፋስ ሀይል የሚመነጭ ኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ በኢትዮሪሶርስ ግሩፕ ተሰርቶ በ2009 ዓ.ም ተመርቋል፡፡ አገልግሎትን ለህብረተሰቡ ከማድረስ ጋር በተያያዘ የአገልግሎት ጥራት፤ የአገልግሎት ክፍያ ፍትሃዊነት እና ተያያዥነት ባላቸው ጉዳዮች ዙሪያ የአከባቢው ህብረተሰብ የሚያነሳቸውን ጥያቄዎች እና አገልግሎት አቅራቢው ድርጅት ከአዋጭነት አንጻር በሚያነሷቸው ጥያቄዎች ላይ መግባባት የሚያስችል ውይይት ተካሂዷል፡፡
የኢትዮጵያ ኢነርጂ ባለስልጣን በኢነርጂ አዋጅ ቁጥር 810/2006 ከተሰጡት ስልጣን እና ሃላፊነት መካከል ከብሄራዊ ግሪድ ጋር ያልተያያዘ ታሪፍን ገምግሞ ማጽደቅ እና የኢነርጂ አገልግሎት አሰጣጥ ደረጃ የማውጣት አገልግሎቱም አስተማማኝ፤ ፍትሃዊና ኤኮኖሚያዊ ማድረግ የሚሉት ይገኙበታል፡፡ ይህንንም መሠረት በማድረግ ባለስልጣን መ/ቤቱ ባቋቋመው ኮሚቴ አማካኝነት ጉዳዩን ከዳር ለማድረስ በመሰራት ላይ ይገኛል፡፡

Print   Email